ኢትዮጵያ ሀገሬ፣ የሺህ ዘመን እናት

ኢትዮጵያ ሀገሬ፣ የሺህ ዘመን እናት

Getish Ayalew

0 j'aime4:5225 oct. 2026

Créée avec HeartMuLa

Créez une chanson comme celle-ci

Transformez un prénom, un souvenir ou vos propres paroles en chanson en quelques minutes.

En faire un cadeau

Prompt

ኢትዮጵያ ሀገሬ፣ የሺህ ዘመን እናት በምሥራቅ አፍሪካ፣ ያበራች ከዋክብት፣ የሰላም ማደሪያ፣ የታሪክ እመቤት፤ የውበትሽ ዜማ፣ በዓለም ሲያስተጋባ፣ ፍቅርሽና ክብርሽ፣ ወደ ልብ ሲገባ… ________________________________________ ወራሪ ሲመጣባት፣ ሉዓላዊነቷን ሊደፍር፣ ልጆቿ ወጡ በአንድነት፣ ድርና ማግ ሆነው ለሀገር፤ በአድዋ ተራሮች ላይ፣ የታሪክ ማህተም ሲታተም፣ የጀግንነት አርማዋ፣ በዓለም ፊት ሲያበራ ዘላለም። የቅኝ ግዛትን ግፍ የዘጋ፣ የአፍሪካን አህጉር ያነቃ፣ የጥቁር ሕዝብ ኩራት ኢትዮጵያ አንቺ ነሽ በቃ! በአረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ፣ ሰንደቅ ዓላማ ያበራ፣ የጀግንነት ታሪኳ፣ እስከ ዘላለም የሚወራ። ኢትዮጵያ ሀገሬ፣ የሺህ ዘመን እናት… ________________________________________ ከዓባይ እስከ ተከዜ፣ ከኦሞ እስከ አዋሽ፣ የተፈጥሮሽ ድንቅ ውበት፣ የለምለም ምድርሽ፤ የአክሱም፣ የላሊበላ፣ የጎንደር ታሪክሽ፣ የቀደመች ሥልጣኔ፣ የዓለም ድንቅ ቅርስሽ። የውሃሽ ገበታ ፈሶ፣ የዓለምን ጥም የሚቆርጥ፣ የለምለም አፈርሽ ፍሬ፣ ለሕዝቦችሽ ፈገግታ የሚሰጥ፤ በታላቅ ሕዳሴሽ ዜማ፣ የተስፋችን ብርሃን በራ፣ የሺህ ዘመን እናት ሀገር፣ ስምሽ በዓለም ተጠራ። ኢትዮጵያ ሀገሬ፣ የሺህ ዘመን እናት… ________________________________________ የተለያዩ ቋንቋዎችና የሕብረ-ብሔር ውበት፣ በአንድ ማዕድ የተቀመጡ፣ በሰላም በፍቅር በፅናት፤ ባህልና ቋንቋሽ አክሊል፣ የልዩነትሽ ጌጥ፣ አንድነታችን ጥንካሬ፣ የማይናወጥ መሠረት። ክርስቲያን ሙስሊሙ በአንድ፣ ተዛዝነው የሚኖሩበት፣ በደስታና በሐዘን፣ እጅ ለእጅ ተያይዘው የሚቆሙበት፤ ልዩነት ውበት ሆኖ፣ አንድነት አለኝታችን፣ የጸናሽ እናት ሀገር፣ የሰላም ማደሪያችን። ኢትዮጵያ ሀገሬ፣ የሺህ ዘመን እናት… ________________________________________ ከቀደሙት አባቶች፣ የተቀበልነውን የአባቶቻችንን አደራ፣ ይህን አንድነት ጠብቀን እናበራዋለን እንደ ከዋክብት ተራ፤ የእናታችንን ክብር፣ በደም የተጻፈ ታሪክ፣ በልባችን አጽንተን እንኖራለን ሐሪክ፤ የሺህ ዘመናት እናት፣ የፍቅርና የፅናት መገኛ፣ የነፃነት ብርሃን የሆንሽ የዓለም መደነቂያ፤ ይህቺን የተባረከች ምድር፣ በእውቀትና በሥራ ስምሽን በዓለም እንድታገንን፣ ለዘላለም እንጠብቅሻለን፣ በፍቅርና በክብር! ________________________________________ ኢትዮጵያ ሀገሬ፣ የሺህ ዘመን እናት፣ በአጥንትና በደም፣ የጸናሽ በፅናት፤ የነፃነት ፋና፣ የታሪክ አክሊላችን፣ ዘላለም ተከብረሽ፣ ኑሪልን እናታችን! ዘላለም ተከብረሽ... ኑሪልን እናታችን!